ጉመር ,ጉራጌ ዞን









የወረዳው አስተዳደር መልዕክት
የጉመር ወረዳ አስተዳደር
ጉመር ወረዳ በጉራጌ ዞን ከሚገኙ 10 ወረዳዎችና 5 ከተማ አስተዳደሮች አንዱ ሲሆን ከዞናችን ከተማ ወልቂጤ በስተምዕራብ 65 km ከሀገሪቱ በደቡብ አቅጣጫ ከአዲስ አበባ 220 km ርቆ ይገኛል።
➔ወረዳችን በ18 የገጠር ቀበሌዎች እና በ2የከተማ ማዘጋጃ ቤቶች (ቦሌ እና ባድ) የተዋቀረ ሲሆን የወረዳችን ዋና ከተማ የሆነው አረቅጥ ከተማ ወደ ከተማ አስተዳደርነት አድጓል። ወረዳችን በሰሜን እዣ ወረዳ፣ በደቡብ ጌታ ወረዳ፣ በምስራቅ ስልጤ ዞን እንዲሁም በምዕራብ ቸሀ ወረዳ ያዋስኑታል።
ሰለ ወረዳው
ውብ እና ማራኪ የተፈጥሮ መስህቦች
በወረዳችን 3 ሀይቆች የሚገኙ ሲሆን አረቅጥ፣ የቦባ እና ደወሼ ሀይቆች በመባል ይታወቃሉ። በእነዚህ ሃይቆች እና በተለያየ ቀበሌዎች በሰራናቸው ኩሬዎች ላይ የአሳ ጫጬት በመጨመር አሳ ማምረተና መመገብ ለገበያ ማቅረብ ጀምረናል።










በወረዳው የሚመረቱ ምርቶች
ገብስ የደጋ ፖም ሮዝመሪ እና የበግ ምርቶች





የቅርብ ጊዜ ዜናዎቻችን
ከድረገጻችን በተጨማሪ ዜናዎቻችን በፌስቡክ ገጻችን እና የቴሌግራም አድራሻችን መከታተል ይችላሉ።
ከነገ ጀምሮ በፕላስቲክ ከረጢት እቃ መያዝም ሆነ መሸጥ በሕግ እንደሚያስቀጣ ያውቃሉ?
ከነገ ጀምሮ በፕላስቲክ ከረጢት እቃ መያዝም ሆነ መሸጥ በሕግ ያስቀጣል። ታዲያ ለገበያ ምን ይዘን እንውጣ? ከቤትዎ ሲወጡ የጨርቅ ከረጢት ወይም ዘላቂ የሆኑ የሸመታ ከረጢቶችን መያዝዎን ያረጋግጡ። ይህ አዲስ መመሪያ የአካባቢ ብክለትን ለመቀነስ ትልቅ እርምጃ ነው። የፕላስቲክ ከረጢቶች በአካባቢ ላይ የሚያደርሱትን ጉዳት ለመቀነስ የሚደረገው ጥረት የሚደነቅ ቢሆንም፣ የኅብረተሰቡን የዕለት ተዕለት ፍላጎት ለማሟላት በቂ ተኪ ምርቶች ተዘጋጅተው […]
በራስ አቅም ችግሮች ለመቋቋምና እንዲሁም ወቅታዊና ቅጽበታዊ አደጋዎችን ለመከላከል በጉራጌ ዞን እየተሰራ ያለው ስራ ለሌሎች አካባቢዎች አስተማሪ እንደሆነ ተገለፀ።
በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽፈት ቤት በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ማዕከል 2ተኛ ዙር የብልጽግና ፓርቲ ስልጠና ላይ እየተሳተፉ ያሉ አመራሮች በጉመር ወረዳ በራስ አቅም ለመጠባበቂያ እህል ክምችት የለማ ማሳ ፣ በበጋ ወራት በተቀናጀ ተፋሰስ በጠረጴዛማ እርከን የለማ መሬት የገብስ ማሳና እንዲሁም የቦባና የአረቅጥ ሐይቅን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት […]
ነሐሴ 07/2017 ዓምየሐረሪ ክልልና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤቶች አባላት በጉራጌ ዞን ጉመር ወረዳ የአበኬ ቀበሌ ጉልቾ…
የሐረሪ ክልልና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤቶች በልምድ ልውውጥ ማጠቃለያ ወቅት በጉራጌ ዞን ጉመር ወረዳ የአበኬ ቀበሌ ጉልቾ ጀፎረ ጎብኝተዋል። በተመሳሳይ በቀበሌው በሚገኝ 93 ሄክታር የማህበረሰብ ጥብቅ ደን ችግኝ ተክለዋል። ምክር ቤቶቹ ጉልቾ ጀፎረን የጎበኙት ችግኝ የተከሉት የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በተገኙበት ሲሆን፤ ጀፈረን አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል። አቶ ላጫ […]
