የሴቶች ቀን

በጉራጌ ብሄረሰብ እንዲሁም በጉመር ወረዳ በርካታ የሚዳሰሱና የማዳሰሱ ባህላዊእሴቶች አሉት፡፡እነዚህ ድንቅ ቱባ ባህሎች ይዘታቸው ሳይቀይሩ ከትውልድ ትውልድ እንዲሸጋገሩ በማድረግ ለትውልድ እየተላለፉ ይገኛሉ፡፡ከእነዚህም ባህላዊ እሴቶች መካከል አንዱ አንትሮሽት ነው፡፡

አንትሮሽት የሴቶች ቀን በጉራጌ ማህበረሰብ እናት በወለደችው ልጅና በባለቤቷ የምትከበርበት በዓል ነው፡፡አንትሮሽት በማህበረሰቡ ዘንድ ያሉትን የመከባበር፣የሰላምእሴቶች እንዲለሙ የሚደረግበትና ሴቶች መብቶቻቸው እንዲያስከብሩ ተጠቃሚነታቸው እንዲያረጋግጡና ባህላዊ እሴቶቻቸው የሚያጠነክሩበት እለት እንደሆነም ይታወቃል፡፡ አንትሮሽት(የሴቶች ቀን )በዓል ከዛሬ ከ250 እስከ 300 ዓመት በፊት በእናቶች የተጀመረ በዓል እንደሆነ ታሪክ ይዘግባል፡፡

አንትሮሽት ወይም የእናቶች ቀን በዓል በዓለም አቀፍ ደረጃ ማርች 8 በማለት የሴቶች የመሪነት ተሟጋች ውጤታማነት ቀን ከመከበሩ አስቀድሞ በዞኑ ውስጥ ያሉ የጉራጌ እናቶች ዘንድ ቀድመው ሴቶች ከወንዶች ጋር እኩል መብት የጠየቁበት፣እረፍት እንደሚያስፈልጋቸው ያወጁበት ቀን መሆኑም መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ይህ የሴቶች ቀን በዓል በእናቶች የተጀመረ በዓል እንደሆነም ይታወቃል፡፡

በዚህ የበዓል ቀን እናቶች አመቱን ሙሉ ከጠዋቱ 12 ሰዓት ምሽት ድረስ እንጨት ሲለቅሙ፣ውሀ ሲቀዱ፣ቆጮ ሲጋግሩ፣አካባቢያቸውንሲያፀዱ፣ሲወልዱ ሲያጠቡና መሰል ተግባራትን ሲከውኑ ከርመው አንድ ቀን በባሎቻቸውና በልጆቻቸው ልናርፍ እና ልንከበር ይገባል በማለት የጥር ወር በገባ መጨረሻ ላይ በዓሉን በድምቀት ይከበራል፡፡በማህበረሰቡ ዘንድ ያሉት የመከባበር፣የሰላም እሴቶችን ይበልጥ እንዲለሙ የሚደረግበትና ሴቶች መብቶቻቸውን እንዲያስከብሩና ተጠቃሚነታቸው እንዲያረጋግጡ እንዲሁም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊና ባህላዊ እሴቶቻቸው የሚያጠናክሩበት እለት ነው፡፡

ጾታዊ እኩልነት ለማስፈን ትግል የሚደረግበት እንዲሁም በሰላም ፣በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታና በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል የበዓሉ መከበር ትልቅ ፋይዳ አለው፡፡በወረዳው ማህበረሰብ ዘንድ ከ250 አመት በፊት የአንትሮሽት በአል ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ይከበራል፡፡እናቶች በዚህ ወቅት ደስታቸው ወደር የሌለውና እናት ከምንም ነገር በላይ የሚያስደስታት ሆዷ ማራስና ቂቤ መቀባት እንደሆነ ይታወቃል፡፡የአንትሮሽት በአል የሚከበረው በአመቱ እናቶች እረፍት እንዲያደርጉ ፣እንዲደሰቱ፣ልጆቻቸው የተለያ ስጦታዎች አዘጋጅተው ለእናታቸው በማበርከት ምርቃት የሚያገኙበት፣የተጣላ የሚታረቅበት፣ባል ሚስቱን የሚያከብርበትና በተራው ምግብ ሰርቶ የሚመግብበት እንዲሁም ለእናቶች የሚታረድ በሬ እንዳቅሙ የሚገዛበት የጎረቤት እናቶችና ሴቶች ተሰብስበው የተለያ የባህል ምግቦች አዘጋጅተው በአሉን በከፍተኛ ድምቀት ያከብሩታል፡፡ይህ ቱባ ባህል ከአምስት መቶ አመት በፊት የነበረ በአል እንደሆነና የበዓሉ ዋና አላማ የእናቶች ቀን ሲሆን እናቶች ደግሞ አመቱን ሙሉ በበርካታ ስራዎች ተጠምደው የሚለፉበት፣የሚደክሙበት እንደሆነና በዚህ በዓል እለት እናቶች እራሳቸውን

የሚያሳርፍበት፣የሚከበሩበት፣በወለደችው ልጅ በባለቤቷ የምትከበርበት በአል ነው፡፡ዘመናዊነት ወይም መጤ የባህል ወረራ ውስጥ በመግባት በአሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ ትንሽ እየተመናመነበትና የተቀዛቀዘበት ሁኔታ እንደነበር ይታወቃል፡፡በአንትሮሽት በአል ለሚታደሙ እናቶች ዝሟሞጃት፣የስጋ ክትፎ፣የጎመን ክትፎ እና ሌሎችም ምግቦች ይቀርባል፡፡አንትሮሽት በማህበረሰቡ ዘንድ ያሉትን የመከባበር፣የሰላም እሴቶች እንዲለሙ የሚደረግበትና ሴቶች መብቶቻቸውን እንዲያስከብሩ፣ተጠቃሚነታቸው እንዲያረጋግጡና ባህላዊ እሴቶቻቸውን የሚያጠናክሩበት እለት እንደሆነም ይታወቃል።