ጉመር ,ጉራጌ ዞን
We Offer Landscaping
Services Provide
Fruit is their fill meat, hath abundantly place meat don't stars and which signs third second
after seasons under fowl day grass. Earth he sea him may shall multiply.
አረቅጥ ሀይቅ
ከወረዳው ዋና ከተማ ከአረቅጥ በስተ ሰሜን ምስራቅ በ1 ከ.ሜ ርቀት ላይ በአረንጓዴ ተክሎች ተከቦ ይገኛል፡፡ሀይቁ መዲናችን ከሆነችው አ.አ 219 ከ.ሜ፣ከሀዋሳ በአንጋጫ መንገድ 220 ከ.ሜ እንዲሁም ከዞኑ መስተዳድር ወልቂጤ ከተማ በ68 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል ፡፡ ከፍታው 2,800 እስከ 2890 ሜ ከበባህር ጠለል በላይ ሲሆን የአረቅጥ ሀይቅ ስፋት 134.5 ሄ/ር የሚሸፍን ሲሆን አማካኝ ጥልቀት 2ሜ ይደርሳል፡፡
ሀይቁን የሚያዋስኑዋት ቀበሌዎች በስተ ምራብ በስተ ሰሜን በከፊል ቡርዳና ደንበር ቀበሌ የግንቤ ሲሆን በስተ ደቡብ አረቅጥ ከተማ በስተ ምስራቅ አ/ሸለቆ እና ምዕራብ እሴን ቀበሌ ያዋስኑዋታል፡፡
ስለ አረቅጥ ቀደምት ታሪክ
ሀይቁ በወረዳው ዋና ከተማ ስም አረቅጥ መጠራት ከጀመረ 110 ዓመት በላይ ሆኖታል፡፡
አረቅጥ የሚለው ቃል አቻ ፍቺ ባይኖረውም በሁለት መንገድ ሲገለጽ ይስተዋላል፡- እነዚህም በአፈታሪክ እና በፅሁፍ ሲሆኑ፤አረቅጥ የሚለው ስያሜ አለቅጥ ከሚለው ቃል የተወሰደ እንደሆነ ታሪክ ያወጋናል፤ ይህም የተባለበት ምክንያት በወቅቱ የሀገራችን መሪ የነበሩት አፄ-ሚኒሊክ ሀገሩን በሚያስገብሩበት ወቅት ወደ ጉራጌ ዞን በመምጣት ዳቁነ መቀመጫቸው አድርገው ጎማረና ጌቶ ለማስገበር ጦራቸው ይልካሉ በዚያም ወቅት አጋዝ ዳርሳሞ የተባሉ የጦር መሪ እንዲህ በማለት ይመክታሉ ‹‹ሰብ በምር የሰብ ይጔብር ቸነኸቢም ባንኼሬ አንቸነብከ›› ማለትም ‹‹ሰው እንዴት ለሰው ይገብራል፤ መጣህብኝ እንጂ አልመጣሁብህም›› በማለት ጦርነት ይገጥማሉ በዚህም ወቅት በጣም ብዙ ህዝብ በቦታው ይሞታል ያም ሲሆን በህይወት የተረፈው የአፄ ሚኒሊክ ወታደር ወደ ዳቁነ በመመለሰ የቀን ውሎ እንዲህ በማለት ዘግቦታል..‹‹ ያለቅጥ ሰው አለቀ!›› በማለት ይነገራል፡፡በሌላ መንገድ አልቅጥ የሚባል ትል በውሃው ውስጥ እንደነበረና ማህበረሰቡ የትልዋ ስም አርቅጥ ብሎ ይጠራ እንደነበር፤ በዚህም መሰረት የከተማና የሀይቁ ስም አረቅጥ ተብሎ እንደተሰየመ በአፈታሪክ የሚወሳ ነው፡፡ እንዲሁም በሌላ ታሪክ የስልጤ ብሄረሰብ በዚህ አካባቢ ሰፈሮ ይኖር ነበር ፡፡
