የጉመር ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት

አቶ እያሱ ማሬ
የጉመር ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ሀላፊ
ተልዕኮ

በወረዳው ፍትህ እንዲሰፍን የመንግስትና የህዝብ ጥቅሞችን እንዲጠበቁ በህገ መንግስቱ ላይ የተደነገጉ ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ ለማስቻል የህብረተሰቡን ጥቃት ህግ በማሳደግ ወንጀል ፈጻሚዎችን ለህግ እንዲቀርቡና ለፈጸሙት ጥፋት በህግ እንዲጠየቁ በማድረግ እንዲሁም የህብረተሰቡን የመደራጀት መብት በማረጋገጥ የመሪነት ሚና በመጫወት የህግ የበላይነትና መልካም አስተዳደር ማስፈን

ራዕይ

በወረዳው በ2022 ዓ/ም ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ተጠብቀው የህግ የበላይነት ተረጋግጦ በአገራችን በአርአያነት ሲጠቀስ የሚችል ፍትህ ሆኖ ማየት

ዕሴቶች
  • የህግ የበላይነት ማረጋገጥ
  • ፍትህ የማግኘት መብትን እናከብራለን እናስከብራለን
  • በታማኝነት በግልጽኝነት በተጠያቂነት እንሰራለን
  • ለህሊናእና ለህግ ተገዢ እንሆናለን
  • በእኩልነትና ፍትሐዊነት እናምናለን
  • በስራችን ለህብረተሰቡ ቀልጣፋ ጥራት ያለው ተደራሽ እና ወጪ ቆጣቢ የፍትህ አገልግሎት እንሰጣለን