ጉመር ,ጉራጌ ዞን
አራት ወረዳዎችን ያለመለመው የዋቤ ገባር ወንዝ
ዋቸበያ
በጉመር ወረዳ ከሚገኙ ድንቅ የተፈጥሮ መስህቦች ውስጥ አንዱ ዋቻበያ ፏፏቴ ነው።ይህ ፏፏቴ በጌታና በጉመር ወረዳዎች ድንበር በጉመር ወረዳ አርሟ ቀበሌ ውስጥ ይገኛል።ውንቐ ወንዝ የዚህ ፏፏቴ መገኛ ነው።
በጥንቱ ባህላዊ የአምልኮ ዘመን:-
ዋቻበያ በጭሽትና በንፗር የዋቅ የአምልኮ ስርአቶች በተለይ ከጌታ ወረዳ የፈኘቅር ቀበሌ ነዋሪዎች እርድ በብዛት የሚከወንበት ስፍራም እንደነበር ይታወቃል።በጉመርና በጌታ ወረዳ አመቱን በሙሉ ከሚፈሱ ወንዞች ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ውንቐ ትልቁ ነው።
ይህ ወንዝ የተለያዩ ገባር ወንዞች እየጨማመረ ቸሃን ወረዳን አቋርጦ ዋቤ ወንዝ መድረሻው ያደርጋል።
በነገራችን ላይ የጉራግኛ የዚህ ዘመኑ ኮከብ አርቲስት ረሻድ ከድር በቁ.2 አልበሙ 3ኛ ላይ ያለ በእነሞርኛ ዘዬ በሚያቀነቅነው ዘፈኑ ውንቐ ወንዝን እንደ እነሞርና ቸሃ መለያ አድርጎ ይገልፀዋል።
እንዲህ እያለ:-
‘ገኛሽ ተገኘኛ ውንቐ ቢባትርኒ
ተወነኹወ ወሄ…’
.የጉራጌ ዞን ወንዞች ከጥንት እኣእከዛሬ ተዘፍኖላቸዋል። በደራሽ የሰውን ህይወት ሲነጥቁ ጎሸም ተደርገዋል
እየጠጣ እያጠጣ እየታጠበ፣እያጠበ እየዋኘ የኖረባቸው ባለገር የልጆቹን ያህል ባይሆን፣ የላሞቹን፣ የጥጆቹን ያህል ይወዳቸዋል።
ውለታቸውን የሚገልፅባቸው የተለያዩ ቃላት፣ ምርቃትና እንክብካቤ፣የሚጥልባቸውን ተስፋና የህይወት ቁርኝት
#Jimat_ጅማት ወደፊት ታስቃኛችኋለች።
ውንቐ ወንዝ መነሻው ጘታ ወረዳ ቢሆንም እየወረደ ጉመርና ጌታ ወረዳዎች ለሁለት ከፍሎ ቸሃና እኖር ወረዳዎች አጠጥቶ ጊቤ ወንዝ ይቀላቀላል።ከጉመር አርሟ ቀበሌ ከጌታ ፈኘቅር ቀበሌ የወንዙ ተጠቃሚ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚኖሩባቸው ናቸው።
