ጉመር ወረዳ

ጉመር ወረዳ በጉራጌ ዞን ከሚገኙ 10 ወረዳዎችና 5 ከተማ አስተዳደሮች አንዱ ሲሆን  ከዞናችን ከተማ ወልቂጤ በስተምዕራብ 65 km ከሀገሪቱ በደቡብ አቅጣጫ ከአዲስ አበባ 220 km ርቆ ይገኛል።

ወረዳችን በ18 የገጠር ቀበሌዎች እና በ2የከተማ ማዘጋጃ ቤቶች (ቦሌ እና ባድ) የተዋቀረ ሲሆን የወረዳችን ዋና ከተማ የሆነው አረቅጥ ከተማ ወደ ከተማ አስተዳደርነት አድጓል። ወረዳችን በሰሜን እዣ ወረዳ፣ በደቡብ ጌታ ወረዳ፣ በምስራቅ ስልጤ ዞን እንዲሁም በምዕራብ ቸሀ ወረዳ ያዋስኑታል።ወረዳችን 233 ካሬ ኪ.ሜ የቆዳ ስፋት ያለው ሲሆን ከባህር ወለል በላይ ከፍታው ከ2500 እስከ 3260 ሜትር የሚደርስና ሙሉ በሙሉ ደጋ የሆነ የአየር ሁኔታ ያለው ወረዳ ነው።

ወረዳችን በ18 የገጠር ቀበሌዎች እና በ2የከተማ ማዘጋጃ ቤቶች (ቦሌ እና ባድ) የተዋቀረ ሲሆን የወረዳችን ዋና ከተማ የሆነው አረቅጥ ከተማ ወደ ከተማ አስተዳደርነት አድጓል። ወረዳችን በሰሜን እዣ ወረዳ፣ በደቡብ ጌታ ወረዳ፣ በምስራቅ ስልጤ ዞን እንዲሁም በምዕራብ ቸሀ ወረዳ ያዋስኑታል።ወረዳችን 233 ካሬ ኪ.ሜ የቆዳ ስፋት ያለው ሲሆን ከባህር ወለል በላይ ከፍታው ከ2500 እስከ 3260 ሜትር የሚደርስና ሙሉ በሙሉ ደጋ የሆነ የአየር ሁኔታ ያለው ወረዳ ነው።  እንደ ማዕከላዊ እስታቲክስ መረጃ መሠረት በ2014 ዓ.ም የወረዳው ህዝብ ብዛት በገጠርና በከተማ ወ=57,506 ሴ=65,354  ድ=122,860 (1መቶ 22ሺህ 860) የደረሰ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 46 በመቶ የሚሆኑት ወንዶች መሆናቸውን መረጃው ያመለክታል።በወረዳች እና በአረቅጥ ከተማ አስተዳደር በድምሩ #1ኮንስትራክሽናኢንድስትሪያል ኮሌጅ፣ #5ሁለተኛ ደ/ትቤቶች #34አንደኛ ደ/ትቤቶች #5ጤናጣቢያዎች #1ቀይ መስቀል መድሃኒት ቤት #1የመብራት አገልግሎት መስጫ ማዕከል ለማህበረሰባችን አገልግሎት ይሰጣሉ።