የአረቅጥ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አቶ ሚፍታ በደዊ የአረቅጥ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን ራዕይ በ2022 ብቁና በሙያው የሚተማመን ዜጋ በማፍራት ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን በመስራት ለህብረተሰቡ በማውረድና ለጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የተሟላ ድጋፍ በመስጠት ፖሊቴክኒክ ሆኖ ማየት ነው፡፡ ተልዕኮ የክልሉ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ስትራቴጂዎችና ዕቅዶች መሰረት በማድረግ ኮሌጁን በሰው ሃይልና በግብዓት በመደራጀት በፍላጎት በገበያ ጥናት ላይ የተመሰረተ ስልጠና በመስጠት ስራ ፈጥሮ ወይም ተቀጥሮ ራሱን ማስተዳደር የሚችል ከዝቅተኛ እስከ መካከለኛ ደረጃ በዕውቀት በክህሎት በአመለካከት የተለወጠና የሰለጠነ የሰው ሃይል በጥራትና በብቃት በማፍራ የአካባቢውን የቴክኖሎጂ ፍላጎት በማሰስ በጊዜ ጉልበትና ገንዘብ ቆጣቢ ቴክኖሎጂዎችን ቀድቶና አሻሽሎ በመስራት በጥ/እ/እንተርፕራይዞች በኩል ለተጠቃሚዎች ማድረስና ለቴክኖሎጂ ሽግግር የተሟላ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ ለኢንተርፕራይዞች በመስጠት የሃገሪቱን የልማት ዕቅዶች ተፈጻሚ እንዲሆኑ ኮሌጁ የራሱን ሚና ይወጣል፡፡ እሴቶች በቡድን መስራት አሳታፊነት ትውልድን መቅረጽ ስርዓተ ጾታ ተኮርነትእኩልነት ፍትሃዊነት ግልጸኝነት ተወዳዳሪነት ተጠያቂነት ሀቀኝነት ለዙጋ ዋጋ መስጠትየህዝብ አገልጋይነት