ወገፐቻ የደን ሀብቶች ወገፐቻ በጉራጌ ከሚገኙ ረጅም ዘመናት ካስቆጠሩት የደን ሀብቶች ከሚገኙበት ስፍራ ውስጥ አንደኛው ነው። በጉመርና ቸሀ ወረዳዎች ድንበር አካባቢ የሚገኝ ተፈጥሯዊና ጥልቅ የሆነ ትውፊታዊ ስርዓትና ታሪክ አዘል የሆነ ውብ ስፍራ ነው።የጉራጌዎች የእውቀት፣ የጥበብና የፍልስፍና ታሪክ መጭለፍያ ባህር÷ የፍትህና የርትዕ ማእከል……የከየትመጣነት፣ የአስተሳሰብ፣ የጀግንነት፣ የፍትህ እና የርትዕ ባህላዊ አሰተዳደር ውቅር መፍለቂያ የማንነት መሠረት ወገፐቻ በሀገር በቀል እፅዋት በተሸፈነው የወገፐቻ ጥቅጥቅ ደን በውስጡ ፅድ ዝግባና የተለያዩ ዛፎች የሚገኙ ሲሆን አእዋፍት፣ ጦጣ፣ጉሬዛና መሠል አራዊቶችም ይገኙበታልም።