የኢንቨስትመንት አማራጮች

ወረዳችን ለግብርና ምቹ የሆነ የአየር ሁኔታ እና መልከአምድር ያለው ሲሆን
-በሰብል ልማት ገብስ፣ ባቄላ፣ አተር በስፋት ይመረታል። ስንዴ በመኸር እና በበጋ መስኖ በስፋት ማምረት ጀምረናል።

በእንስሳት ዘርፍ ለከብት እርባታ፣ ለበግ እርባታ፣ ለዶሮ እርባታ፣ ለንብ ማነብ፣ ለአሳ ማስገር የተመቸ ነው።

በአትክልትና ፍራፍሬ ፖም፣ ፕሪም፣ ድንች፣ ካሮት፣ የሃበሻ ጎመን የመሳሰሉት በስፋት ይመረታል።

ሙሉወርቅ ሪዞርትና ሆቴል

በጉራጌ ዞን በጉመር ወረዳ በአረቅጥ ከተማሀይቅ ዳር ተገንብቶ የሚገኝ እና ተፈጥሯዊ የመዝናኛ ስፋራ የሚገኝበት ሲሆን ከአዲስ አበባ በ220 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል ፣የመሮጫ ቦታ፤ ረጅም የወክዌይ ቦታ፣የጀልባ ጉዞ፣ የኳስ መጫወቻ ሜዳ፣መፀሃፍ ማንበቢያ ቦታ፣፣ የልጆች መጫወቻ፣ አሳ ማጥመድ እና የጓሮ አትክልት ከብዙ በጥቂቶቹ ናቸው፣