የጉመር ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት አቶ ጅላሉ ሻፊ የጉመር ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ሀላፊ ዓላማ በወረዳው ተወዳዳሪና ብቁ የሆነ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ በመፍጠር፣በከተሞች የአካባቢ ልማትን በማፋጠን፣የከተማ-ከተማና የከተማ-ገጠር ትስስርን በማጠናከር ለከተማ ልማት ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ከተሜነትን ማሳደግና ዘላቂ የሆነ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ልማት ማረጋገጥ ነው፡፡ ራዕይ በ2022 በወረዳው ተወዳዳሪ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ በመገንባት ከተሞች ምርታማና የብልጽግና ማዕከል ሆነው ማየት ነው፡፡ ተልእኮ በወረዳው የሚገነቡ ግንባታዎች ወጪ ቆጣቢና ጥራቱ የተጠበቀ፣ከተሞችን በፕላን በመምራት፣ የመሬት አቅርቦት እና አስተዳደርን ግልጽ ቀልጣፋና ፍትሃዊ በማድረግ፣የቤትና መሠረተ ልማት አቅርቦት በማሳደግ፣አረንጓዴ ልማት በማረጋገጥ ከተሜነትን በማስፋፋት ክፍለ ኢኮኖሚውን ማሳደግ ነው፡፡ የሴክተሩ ዕሴቶች የመንግስት ፖሊሲና ስትራቴጂ የዕቅዶቻችን መርሆዎች ናቸው፣የሰው ኃይል ካሉን ሀብቶች ሁሉ ትልቁ ሀብታችን ነው፣በማያቋርጥ ለውጥና መሻሻል እናምናለንተገልጋዮቻችን የሕልውናችን መሠረት ናቸው!ቅሬታ አቅራቢዎች መካሪዎቻችን ናቸው፣