ነሐሴ 07/2017 ዓምየሐረሪ ክልልና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤቶች አባላት በጉራጌ ዞን ጉመር ወረዳ የአበኬ ቀበሌ ጉልቾ ጀፎረ ጎበኙ።

የሐረሪ ክልልና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤቶች በልምድ ልውውጥ ማጠቃለያ ወቅት በጉራጌ ዞን ጉመር ወረዳ የአበኬ ቀበሌ ጉልቾ ጀፎረ ጎብኝተዋል።

በተመሳሳይ በቀበሌው በሚገኝ 93 ሄክታር የማህበረሰብ ጥብቅ ደን ችግኝ ተክለዋል።

ምክር ቤቶቹ ጉልቾ ጀፎረን የጎበኙት ችግኝ የተከሉት የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በተገኙበት ሲሆን፤ ጀፈረን አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

አቶ ላጫ በማብራሪያቸው ጀፎረ የቆየ የጉራጌ እሴት እና ማህበራዊ ጉዳዮችን መከወኛ መሆኑን ገልጸው ተሞክሮው ወደሌሎች አከባቢ መስፋት ይኖርበታል ብለዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ በረከት ከድር የሐረሪ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በክልሉ ያደረጉት ልምድ ልውውጥ የዳበረና ጤናማ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት ማሳያ እንደሆነ ገልጸዋል።

የሐረሪ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ወይዘሮ ሀሰናት ሙሜን ጨምሮ ያነጋገርናቸው የምክር ቤት አባላት ከልምድ ልውውጡ ብዙ መማራቸውንና በጀፎረ መደመማቸው ገልጸውልናል።

መረጃው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
ኮሙኒኬሽን ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *