በኢፍድሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የተመራው ሉኡክ በጉራጌ ዞን በጉመር ወረዳ በመገኘት የጤና የልማት ስራዎች ጎብኝተዋል ።

በጉብኝቱም በጉመር ወረዳ የእንጀፎ ቀበሌ መሠረታዊ የጤና ኬላ ፓኬጅ አተገባበር እና የሞዴል ቤተሰብ ጤና እንክብካቤ የተሰሩ ስራዎች የቤት ለቤት ምልከታ ተደርጓል ፡፡በኢፍድሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ እንደገለጹት በክልሉ እየተሰሩ ያሉ የጤና ስራዎች ማህበረሰቡ በጤናው ዘርፍ ተጠቃሚነቱን ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱ መሆናቸው ገልፀዋል።

በጉመር ወረዳ በእንጀፎ በቀበሌው ተዛዙረው ያዩት መሰረታዊ ጤና ኬላ የአገልግሎት አሰጣጥና የሞዴል ቤተሰብ ጤና እንክብካቤ የተሰሩ ስራዎች አስደሳች በመሆናቸው በቀጣይ ተጠናክሮ ሊቀጥሉ እንደሚገባ አንስተው በማህበረሰቡ የሚነሱ የጤና ችግሮች ከክልል ፣ከዞንና ከወረዳ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ችግሮች እንዲፈቱ ይደረጋል ብለዋል።የጉመር ወረዳ ዋና አስተዳደር አቶ ደሳለኝ ከድር የእንኳን መጣችሁ መልእክት ባስተላለፉበት ወቅት እንደገለጹት መንግስት የህዝባችን ጤና ለማበልፀግ የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ጥራት ለማሻሻልና እያደገ የመጣው የማህበረሰብ ፍላጎት ለማሟላትና ቀልጣፋና ውጤታማ የጤና ኤክስቴንሽን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸው ተናግረዋል።

በጤናው ዘርፍ የነበሩ ችግሮች ለመፍታት አዲስ የጤና ኤክስቴሽን ፍኖተ ካርታ እንደ ወረዳ በተደረገው እንቅስቃሴ አበረታች ውጤቶች ተገኝቷል ብለዋል ፡፡

በወረዳ አገልግሎት ላይ የነበሩ ጤና ኬላዎች በአዲሱ የጤና ጤክስቴሽን ፍኖተ ካርታ የምደባ መስፈርቶች መሠረት መለያታቸው ጠቁመው ዛሬ የተጎበኘው የእንጀፎ ቀበሌ መሠረታዊ ጤና ኬላ በወረዳው መንግስት በህብረተሰቡ እና በሌሎች ባለድርሻ አካላት አስተዋፆ የተሰራ ሲሆን ግንባታው በእስታንደርዱ መሠረት ለማድረስ ቀሪ ስራው ህዝባችን በማሳተፍ የሚፈጸም መሆኑን አንስተዋል ።

የወረዳችን ህዝብ በጤናው ዘርፍ በሚከናወኑ አጠቃላይ ስራዎች የተለያዩ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አንስተው በሀገረ ደረጃ ፍትሀዊ የሆነ ጤና ለሁሉም ለማድረስ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አባል በመሆን በስፋት እየተሳተፈና ለዘርፉ ውጤታማነት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል ብለዋል ።አክለውም በወረዳው ህዝብ ዘንድ ለብዙ ጊዜ የሚነሳ የሆስፒታል ጥያቄ መንግስት በእቅድ እንደሚመልስ ከህዝባችን በመግባት በትግስት እየጠበቀ ይገኛልያሉት አቶ ደሳለኝ በወረዳችን በሚገኙ ጤና ጣቢያዎች እጅግ ከፍተኛ የሆነ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች እና የመድኃኒት እጥረት ስላለባቸው ህዝባችን ተገቢውን የህክምና አገልግሎት ማግኘት አለመቻሉን ተናግረዋል ።በጉብኝቱም የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዳይሬክተር ዶክተር አብዱልቃድር ገልጋሎ፣ የጤና ሚንስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ድጉማ፣ የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ፣ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ፣ የጉራጌ ዞን አመራሮች ፣የጉመር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደሳለኝ ከድር ጨምሮ የወረዳው የስራ ኃላፊዎች፣ የእንጀፎ ቀበሌ የህብረተሰቡ ክፍሎች ተገኝተዋል ሲል የጉመር ወረዳ የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *