ጉመር ,ጉራጌ ዞን
በኢፌድሪ የገንዘብ ሚኒስቴር አቶ አህመድ ሽዴ የሚመራ የልኡካን ቡድን በጉራጌ ዞን በጉመር ወረዳ በመገኘት የልማት ስራዎች ጉብኝት አደረጉ።
በጉብኝቱም በጉመር ወረዳ በአምዶም እና በድርቦና ሰነን ቀበሌ በመገኘት በ50 ሄክታር መሬት የለማው ሰፊ የገብስ ማሳ ጉብኝት አድርገዋል።አቶ አህመድ ሽዴ በጉብኝታቸው ወቅት ባደረጉት ንግግር በግብርናው ዘርፍ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋል።በዞኑ በሁሉም ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው ያሉት ሚኒስትሩ በተለይ በግብርናው ዘርፍ እየታየ ያለው አመርቂ ውጤት ተስፋ ሰጪና ለወደፊቱም ለስራ የሚያነሳሳ ነው ሲሉ ገልፀዋል።
በግብርና፣በከተማ ልማት እና በየኢንዱስትሪው ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት ሀገሪቱ የጀመረችውን የእድገት ጉዞ የሚያጠናክሩ መሆኑን ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።
ዞኑ ካለው የመልማት አቅም አንጻር በልማት ስራዎች ላይ የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ሚኒስትሩ አመላክተዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፕሬዝዳንት ዋና አማካሪና ልዩ ረዳት አቶ ንጉሴ አስረስ በሰጡት አስተያየትም የኢኮኖሚ ምሰሶ የሆነው ግብርና እመርታ እያሳየ መሆኑን መመልከታቸውን ገልፀዋል።
አክለውም ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ እያስመዘገበች ያለው ለውጥ ልምድ ሊቀሰምበት የሚያስችልና ወደፊት ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባመሆኑን አብራርተዋል፡፡
በዞኑ ብሎም በወረዳው እየተሰሩ ያሉ ሰፋፊ የግብርና ስራዎች የማህበረሰቡን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥና የኑሮ ደረጃ በማሻሻሉ እረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ እንደሆነም አቶ ንጉሴ ገልፀዋል።


በክልሉ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር እየተደረገ ያለውን ጥረት ውጤታማ ለማድረግ የጉመር ወረዳ አርሶ አደሮች አዳዲስ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም እያለሙ መሆኑንም ተገልፆዋል ።በወረዳው አዳዲስ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም በመቻሉ በገብስ፣ በስንዴ ፣በጥራጥሬ እና በሌሎች ሰብሎች የተሸፈነው መሬት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለውም ተመላክቷልበጉብኝቱም በገንዘብ ሚኒስተሩ በአቶ አህመድ ሽዴ በተመራው በዚህ ሉኡክ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳድር ልዩ አማካሪ አቶ ንጉሴ አስረስ የጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ አለማየሁ ገ/መስቀል ፣ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ የዞንና የጉመር ወረዳ የፊት አመራሮች ተገኝተዋል ሲል የዘገበው የጉመር ወረዳ የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው፡፡

ይህ ፕላትፎርም የጉመርና አጠቃላይ የጉራጌን ባህልና አኗኗር እንዲሁም መልካምድራዊ አቀማመጡን ያለውን ተፈጥሮአዊ ውበቱን ይበለጥ ጎላ ብሎ እንዲታይ ለማድረግ እጅግ በጣም የተሻለና አማራጭ የሌለው በመሆኑ በእውነቱ ይህን website እውን እንዲሆን ሀሳባችሁንና እወቀታችሁን እንዲሁም ጊዜያችሁን አስተዋጽኦ ላደረጋችሁ ባለድርሻዎች ከልብ ልትመሰገኑ ይገባችኋል።
ይህ በእንዲህ ሆኖ ይህ website በሰዎች ዘንድ በጣም ተወዳጅ ማራኪ ተፈላጊና ብዙ እይታ ሊኖረው የሚችለው ግን ከምንም አይነት ፖለቲካዊ አሰራር የፀዳ የፓርቲዎች ፕሮፖጋንዳ የማይነዛና በየሚዲያው የሚታዩት ወቅታዊ ዜኖዎችን የማይንፀባረቁበት ከሆነ ብቻ ነው ።