ጉመር ,ጉራጌ ዞን
ፅዱ መንደር ለጤና ተስማሚ አካባቢ በመፍጠር ጤናችንን እንጠብቅ
በጉመር ወረዳ በአረቅጥ ሸለቆ ቀበሌ ” ፅዱ መንደር ለጤና ተስማሚ አካባቢ በመፍጠር ጤናችንን እንጠብቅ” በሚል የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የምረቃ ፕሮግራም ተካሄዷል።
የጉመር ወረዳ ዋና አስተዳደር አቶ ደሳለኝ ከድር በመድረኩ እንደገለጹት በጤናው ዘርፍ በሽታን አሰቀድሞ መከላከል መሰረት ያደረገው የጤና ፖሊሲ ተግባራዊ በማድረግ በቀበሌው ሁሉም የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጆች ተግባራዊ በማድረግ እያንዳንዱ መንደር ፅዱ ውብና ማራኪ የሆኑ መንደር ለመፍጠር የተሰራው ስራ የተሻሉ በመሆናቸው በቀጣይ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም ተናግረዋል።
አክለውም በቀበሌው በዳሳ ወርቸ መንደር የግል፣እና የወል ሽንት ቤቶች ዘመናዊ በሆነ መልኩ በመስራት ሜዳ ላይ ከመጸዳዳት ነጻ የሆነ ቀበሌ ለመፍጠር በማህበረሰብ የተሰራው ስራ በመንደሩን ተዛዙረው በማየት ማረጋገጥ መቻላቸው አንስተው ይህ የተጀመረው የጽዱ መንደር ተግባር የበለጠ በማጠናከር ማስቀጠል እንደሚገባ ጠቁመዋል።
የጉመር ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ ስፍር በበኩላቸው በዘንድሮ አመት ጽዱ መንደር ለጤና ተስማሚ አካባቢ በመፍጠር ጤናችን እንጠብቅ በሚል መሪ ሀሳብ እንደወረዳ የተጠናከረ ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
ማህበረሰቡ የግልና የአካባቢው ንጽህና በመጠበቅ ፅዱ መንደር በመፍጠር ጤና የተጠበቀ አምራች ማህበረሰብ መፍጠር እንደሚገባ ተናግረዋል።
ታመን ለህክምና የምናወጣው ወጪ ለመቀነስና ሙሉ ጤንነታችንን ለማስጠበቅ ወሳኙ ከአይነ ምድር የጸዳ አካባቢ በመፍጠር እና እናቶች ቤት ውስጥ እንዳይወልዱ እየተሰራ ያለው ተግባር አጠናክሮ መቀጠ ያስፈልጋል ብለዋል።
የተሻሻሉ መፀዳጃ ቤት ማህበረሰቡ አቅሙ በሚችለው መልኩ በመገንባት የአካባቢ ንጽህናን የመጠበቅ ተግባርን ትኩረት ሰጥቶ በመስራት በጤናው ላይ የሚመጡ ተላላፊ የሆኑ በሽታዎችን በማስቀረት ጤናው የተጠበቀ ማህበረሰብ ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ ገልፀዋል።
ዛሬ በአረቅጥ ሸለቆ በቀበሌ በዳሰ ወርቸ መንደር የታየው ከአይነ ምድር የጸዳ መንደር መፍጠር መቻሉን በማረጋገጥ መቻላቸው አንስተው በቀጣይም በቀበለ በሁሉም መንደሮች በማህበረሰብ የተጀመረው የተሻሻሉ መጸዳጃ ቤቶች ተጠቃሚነት ለማስቀጠል በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ቀበሌው በጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጅ አተገባበር እና ከአይነ ምድር የጸዳ መንደር መፍጠር ጽዱ መንደር በመፍጠሯ የእውቅና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል ሲል የዘገበው የጉመር ወረዳ መንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።
