ጉመር ,ጉራጌ ዞን









የወረዳው አስተዳደር መልዕክት
የጉመር ወረዳ አስተዳደር
ጉመር ወረዳ በጉራጌ ዞን ከሚገኙ 10 ወረዳዎችና 5 ከተማ አስተዳደሮች አንዱ ሲሆን ከዞናችን ከተማ ወልቂጤ በስተምዕራብ 65 km ከሀገሪቱ በደቡብ አቅጣጫ ከአዲስ አበባ 220 km ርቆ ይገኛል።
➔ወረዳችን በ18 የገጠር ቀበሌዎች እና በ2የከተማ ማዘጋጃ ቤቶች (ቦሌ እና ባድ) የተዋቀረ ሲሆን የወረዳችን ዋና ከተማ የሆነው አረቅጥ ከተማ ወደ ከተማ አስተዳደርነት አድጓል። ወረዳችን በሰሜን እዣ ወረዳ፣ በደቡብ ጌታ ወረዳ፣ በምስራቅ ስልጤ ዞን እንዲሁም በምዕራብ ቸሀ ወረዳ ያዋስኑታል።
ሰለ ወረዳው
ውብ እና ማራኪ የተፈጥሮ መስህቦች
በወረዳችን 3 ሀይቆች የሚገኙ ሲሆን አረቅጥ፣ የቦባ እና ደወሼ ሀይቆች በመባል ይታወቃሉ። በእነዚህ ሃይቆች እና በተለያየ ቀበሌዎች በሰራናቸው ኩሬዎች ላይ የአሳ ጫጬት በመጨመር አሳ ማምረተና መመገብ ለገበያ ማቅረብ ጀምረናል።










በወረዳው የሚመረቱ ምርቶች
ገብስ የደጋ ፖም ሮዝመሪ እና የበግ ምርቶች





የቅርብ ጊዜ ዜናዎቻችን
ከድረገጻችን በተጨማሪ ዜናዎቻችን በፌስቡክ ገጻችን እና የቴሌግራም አድራሻችን መከታተል ይችላሉ።
ነሐሴ 07/2017 ዓምየሐረሪ ክልልና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤቶች አባላት በጉራጌ ዞን ጉመር ወረዳ የአበኬ ቀበሌ ጉልቾ…
የሐረሪ ክልልና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤቶች በልምድ ልውውጥ ማጠቃለያ ወቅት በጉራጌ ዞን ጉመር ወረዳ የአበኬ ቀበሌ ጉልቾ ጀፎረ ጎብኝተዋል። በተመሳሳይ በቀበሌው በሚገኝ 93 ሄክታር የማህበረሰብ ጥብቅ ደን ችግኝ ተክለዋል። ምክር ቤቶቹ ጉልቾ ጀፎረን የጎበኙት ችግኝ የተከሉት የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በተገኙበት ሲሆን፤ ጀፈረን አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል። አቶ ላጫ […]
በኢፍድሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የተመራው ሉኡክ በጉራጌ ዞን በጉመር ወረዳ በመገኘት የጤና የልማት ስራዎች ጎብኝተዋል ።
በጉብኝቱም በጉመር ወረዳ የእንጀፎ ቀበሌ መሠረታዊ የጤና ኬላ ፓኬጅ አተገባበር እና የሞዴል ቤተሰብ ጤና እንክብካቤ የተሰሩ ስራዎች የቤት ለቤት ምልከታ ተደርጓል ፡፡በኢፍድሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ እንደገለጹት በክልሉ እየተሰሩ ያሉ የጤና ስራዎች ማህበረሰቡ በጤናው ዘርፍ ተጠቃሚነቱን ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱ መሆናቸው ገልፀዋል። በጉመር ወረዳ በእንጀፎ በቀበሌው ተዛዙረው ያዩት መሰረታዊ ጤና ኬላ የአገልግሎት አሰጣጥና […]
በኢፌድሪ የገንዘብ ሚኒስቴር አቶ አህመድ ሽዴ የሚመራ የልኡካን ቡድን በጉራጌ ዞን በጉመር ወረዳ በመገኘት የልማት ስራዎች ጉብኝት አደረጉ።
በጉብኝቱም በጉመር ወረዳ በአምዶም እና በድርቦና ሰነን ቀበሌ በመገኘት በ50 ሄክታር መሬት የለማው ሰፊ የገብስ ማሳ ጉብኝት አድርገዋል።አቶ አህመድ ሽዴ በጉብኝታቸው ወቅት ባደረጉት ንግግር በግብርናው ዘርፍ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋል።በዞኑ በሁሉም ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው ያሉት ሚኒስትሩ በተለይ በግብርናው ዘርፍ እየታየ ያለው አመርቂ ውጤት ተስፋ ሰጪና ለወደፊቱም ለስራ የሚያነሳሳ ነው ሲሉ ገልፀዋል። […]
